More

    ቤተክርስቲያን የማፍረስ ዘመቻ በድሬደዋ

    on

    |

    views

    and

    comments

    ባለፈው ሳምንት በድሬደዋ መካነ እየሱስ ቤተክርስቲያን እና በከተማ ከንቲባ ጽ/ቤቱ መካከል ተፈጥሮ የነበረው ችግር በውይይት መፈታቱን ቤተክርስቲያኗ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግራለች፡፡
    ቤተክርስቲያኗ ትፍረስ በሚል ላወጣው ደብዳቤም የከንቲባ ጸ/ቤቱ ቤተክርስቲያኗን ይቅርታ መጠየቁን እና ሁሉም ነገር በንግግር እንደሚፈታ መናገሩን አስታውቃለች፡፡

    በተደረገው ንግግርም ቤተክርስቲኗ የያዘችውን ይዞታ ማልማት ከቻለች በቦታው እንድትቀጥል ካልሆነ ግን የከንቲባ ጸ/ቤቱ ተለዋጭ ቦታ ላይ የምትክ ቤት ሰርቶ እንደሚሰጥ ቃል መግባቱን የቤተክርስቲያኗ ሰብሳቢ አቶ በለሳቸው አምባሮ ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡
    ከቦታው ተነስቶ ወደ ተለዋጭ ቦታ መሄዱም ቢሆን ከቤተክርስቲያኗ መሪዎች ጋር በመነጋገር ብቻ እንደሆነ መተማመን ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል፡፡

    ቀደም ሲል የተላከው ደብዳቤም ቤተክርስቲያነኗ ዙሪያ ላይ ላሉ ተቋማት የተዘጋጀ መሆኑን ከንቲባው መናገራቸውን የገለጹት የቤተክርስቲኗ ሰብሳቢ ይቅርታ መጠየቃቸውንም አነስተዋል፡፡
    ስለሆነም ከተቀመጡት ሁለት አማራጮች መካከል ቤተክርስቲያኗ የፈለገችውን መምረጥ እንደምትችል የከንቲባ ጸ/ቤቱ ገልጿል፡፡

    በሚቀጥለው ሰኞ ከድሬደዋ ከንቲባ ጋር ለመነጋገር ዋናው ሲኖዶስ ከአዲስ አበባ ወደ ድሬደዋ እንደሚያመራ የተገለጸ ሲሆን ከሚደረገው ሰፊ ውይይት በኋላ ቤተክርስቲያኗ የሚበጃትን ትምርጣለች ብለዋል፡፡

    በመጨረሻም የከተማ ከንቲባ ጽ/ቤቱ ጥፋቱን አምኖ ይቅርታ መጠየቅ በመቻሉ ቤተክርስቲያኗ በጣም እንደምታመሰግን የቤተክርስቲያኗ ሰብሳቢ አቶ በላቸው አምባሮ አስታውቀዋል፡፡

    Share this
    Tags

    Must-read

    veronica Adane unable to perform

    Veronica Adane announced that she was unable to perform due to illness. It is known that Veronica Adane has recently entered America to perform her...

    The Red Sea is Ethiopia’s only breath – Prime Minister Abiy

    According to the prime minister in his explanation regarding the port, we want the entire people of Ethiopia, countries in the Horn of...

    የየመኑ ሁቲ የጋዛውን ጦርነት መቀላቀሉን አስታወቀ

    የየመኑ ሁቲ የጋዛውን ጦርነት መቀላቀሉን አስታወቀ፡፡ የመንን እየገዛ ያለው ሁቲ እስራኤል ላይ የድሮንና የሚሳኤል ጥቃት በመፈፀም አጋርነቱን ለፍልስጤማውያን እያሳየ ነው።ቡድኑ እስራኤልን ለመዋጋት ዝግጁ መሆኑንም...
    spot_img

    Recent articles

    More like this

    LEAVE A REPLY

    Please enter your comment!
    Please enter your name here