Home Uncategorized Newes ቤተክርስቲያን የማፍረስ ዘመቻ በድሬደዋ

ቤተክርስቲያን የማፍረስ ዘመቻ በድሬደዋ

0

ባለፈው ሳምንት በድሬደዋ መካነ እየሱስ ቤተክርስቲያን እና በከተማ ከንቲባ ጽ/ቤቱ መካከል ተፈጥሮ የነበረው ችግር በውይይት መፈታቱን ቤተክርስቲያኗ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግራለች፡፡
ቤተክርስቲያኗ ትፍረስ በሚል ላወጣው ደብዳቤም የከንቲባ ጸ/ቤቱ ቤተክርስቲያኗን ይቅርታ መጠየቁን እና ሁሉም ነገር በንግግር እንደሚፈታ መናገሩን አስታውቃለች፡፡

በተደረገው ንግግርም ቤተክርስቲኗ የያዘችውን ይዞታ ማልማት ከቻለች በቦታው እንድትቀጥል ካልሆነ ግን የከንቲባ ጸ/ቤቱ ተለዋጭ ቦታ ላይ የምትክ ቤት ሰርቶ እንደሚሰጥ ቃል መግባቱን የቤተክርስቲያኗ ሰብሳቢ አቶ በለሳቸው አምባሮ ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡
ከቦታው ተነስቶ ወደ ተለዋጭ ቦታ መሄዱም ቢሆን ከቤተክርስቲያኗ መሪዎች ጋር በመነጋገር ብቻ እንደሆነ መተማመን ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል፡፡

ቀደም ሲል የተላከው ደብዳቤም ቤተክርስቲያነኗ ዙሪያ ላይ ላሉ ተቋማት የተዘጋጀ መሆኑን ከንቲባው መናገራቸውን የገለጹት የቤተክርስቲኗ ሰብሳቢ ይቅርታ መጠየቃቸውንም አነስተዋል፡፡
ስለሆነም ከተቀመጡት ሁለት አማራጮች መካከል ቤተክርስቲያኗ የፈለገችውን መምረጥ እንደምትችል የከንቲባ ጸ/ቤቱ ገልጿል፡፡

በሚቀጥለው ሰኞ ከድሬደዋ ከንቲባ ጋር ለመነጋገር ዋናው ሲኖዶስ ከአዲስ አበባ ወደ ድሬደዋ እንደሚያመራ የተገለጸ ሲሆን ከሚደረገው ሰፊ ውይይት በኋላ ቤተክርስቲያኗ የሚበጃትን ትምርጣለች ብለዋል፡፡

በመጨረሻም የከተማ ከንቲባ ጽ/ቤቱ ጥፋቱን አምኖ ይቅርታ መጠየቅ በመቻሉ ቤተክርስቲያኗ በጣም እንደምታመሰግን የቤተክርስቲያኗ ሰብሳቢ አቶ በላቸው አምባሮ አስታውቀዋል፡፡

NO COMMENTS

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Exit mobile version