ሊዮኔል ሜሲ ለ8ኛ ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊ ሆነ
ሊዮኔል አንደሬስ ሜሲ የ2023 ባሎንዶር ሽልማት አሸናፊ ሆኗል፡፡
የ2022/ 2023 የባላንዶር አሸናፊ ሽልማት ሥነ- ሥርዓት በዛሬው ዕለት በፈረንሳይ መዲና ፓሪስ ተካሂዷል፡፡
በዚህም በወንዶች አርጀንቲናዊው የፊት መስመር አጥቂ ሊዮኔል ሜሲ የዓለማችን ምርጥ ተጫዋች በመባል ለ8ኛ ጊዜ የባሎንዶር ሽልማትን
ተቀዳጅቷል፡፡
ለአሜሪካው ኢንተር ሚያሚ እየተጫወተ የሚገኘው ሊዮኔል ሜሲ በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ከአርጀንቲና ብሄራዊ ቡድን ጋር የዓለም ሻምፒዮን መሆኑ ይታወሳል፡፡
በሴቶች ደግሞ ስፔናዊቷ ኮከብ አይታና ቦንማቲ የባላንዶር አሸናፊ መሆን ችላለች፡፡
የ25 ዓመቷ ቦንማቲ ከስፔን ብሔራዊ ቡድን ጋር የሴቶች ዓለም ዋንጫን አሸንፋለች፡፡
በሌላ በኩል የማንችስተር ሲቲው አጥቂ ኧርሊንግ ሃላንድ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ለሆኑ ተጫዋቾች የሚሰጠውን “የገርድ ሙለር” ሽልማት ሲያሸንፍ÷የአስቶን ቪላው ግብ ጠባቂ ኤሚ ማርቲኔዝ ለምርጥ ግብ ጠባቂ የሚሰጠውን “የያሲን ትሮፊ” አሸናፊ ሆኗል።
የሪያል ማድሪዱ የመሐል ሜዳ ተጫዋች ጁድ ቤሊንግሃም ከ21 ዓመት በታች ላሉ ታዳጊ ተጫዋቾች የሚሰጠውን” ኮፓ ትሮፊ” አሸንፏል።