የየመኑ ሁቲ የጋዛውን ጦርነት መቀላቀሉን አስታወቀ፡፡ የመንን እየገዛ ያለው ሁቲ እስራኤል ላይ የድሮንና የሚሳኤል ጥቃት በመፈፀም አጋርነቱን ለፍልስጤማውያን እያሳየ ነው።ቡድኑ እስራኤልን ለመዋጋት ዝግጁ መሆኑንም በግልጽ አስታውቋል።የጦሩ መሪ እንዳስታወቁት ፣እስራኤል ላይ ያነጣጠረ የድሮንና የሚሳኤል ጥቃቶችን ጀምረናል ብለዋል።እስራኤል በጋዛ እየወሰደች ያለችውን ጥቃት እስከምታቆም ድረስ፣ የተቀናጀና መጠነ ሰፊ የአየር ጥቃቶችን እንደሚወስድ የመንን እያስተዳደረ የሚገኘው የሁቲ ጦር ገልጿል።የእስራኤል ሃማስ ጦርነት ከተለኮሰ ጀምሮ የሁቲ ጦር ሶስት ጊዜ ወደ እስራኤል ሮኬት ማስወንጠፉ ታውቋል።ይህንንም ተከትሎ የጋዛው ጦርነት ይስፋፋል በሚል ትልቅ ስጋት መደቀኑን አርቲ ኒውስ ዘግቧ